20 “አሮን በሚቀባበት+ ቀን እሱና ወንዶች ልጆቹ ለይሖዋ የሚያቀርቡት መባ ይህ ነው፦ የኢፍ አንድ አሥረኛ+ የላመ ዱቄት በቋሚነት የሚቀርብ የእህል መባ አድርገው ያቅርቡ፤+ ግማሹን ጠዋት፣ ግማሹን ደግሞ ምሽት ላይ ያቅርቡ። 21 በዘይት ከተለወሰ በኋላም በምጣድ ላይ ይጋገራል።+ ከዚያም በደንብ በዘይት ለውሰህ ታመጣዋለህ፤ የተጋገረውንም የእህል መባ ቆራርሰህ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ይሆን ዘንድ ለይሖዋ ታቀርበዋለህ።