40 ተጨቅጭቆ በተጠለለ አንድ አራተኛ ሂን ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አንድ አሥረኛ የላመ ዱቄትና ለመጠጥ መባ የሚሆን አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ ከመጀመሪያው የበግ ጠቦት ጋር ይቅረብ። 41 ሁለተኛውንም የበግ ጠቦት ልክ ማለዳ ላይ ከምታቀርባቸው ጋር ተመሳሳይ ከሆኑ የእህልና የመጠጥ መባዎች ጋር አመሻሹ ላይ ታቀርበዋለህ። ይህን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርገህ ታቀርበዋለህ።