-
ዘሌዋውያን 3:3-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 እሱም ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤+ ይኸውም አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣+ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ፣ 4 ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያቀርባል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳዋል።+ 5 የአሮን ወንዶች ልጆችም በመሠዊያው ላይ ይኸውም በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ ላይ ያጨሱታል፤+ ይህም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ነው።+
-