29 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የኅብረት መሥዋዕቱን ለይሖዋ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ከኅብረት መሥዋዕቱ መባ ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ ያቀርባል።+ 30 እሱም ስቡን+ ከፍርምባው ጋር ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ እንዲሆን በራሱ እጆች ያመጣል፤ የሚወዘወዝ መባ+ አድርጎም በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዘውዘዋል። 31 ካህኑ ስቡን በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል፤+ ፍርምባው ግን የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ይሆናል።+