7 “‘የበደል መባ ሕግ ይህ ነው፦+ ይህ እጅግ የተቀደሰ ነገር ነው። 2 ለበደል መባ የሚሆነውን እንስሳ፣ ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን እንስሳ በሚያርዱበት ቦታ ያርዱታል፤ ደሙም+ በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ መረጨት ይኖርበታል።+ 3 ስቡን በሙሉ ይኸውም ላቱን፣ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣+ 4 ሁለቱን ኩላሊቶች፣ በሽንጡ አካባቢ ካለው ስባቸው ጋር ያቅርብ። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳዋል።+