-
ዘፀአት 29:10-14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 “ከዚያም ወይፈኑን በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ታቀርበዋለህ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በወይፈኑ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጭናሉ።+ 11 ወይፈኑንም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በይሖዋ ፊት እረደው።+ 12 ከወይፈኑም ደም ላይ የተወሰነውን ወስደህ በጣትህ በመሠዊያው ቀንዶች+ ላይ አድርግ፤ የቀረውንም ደም በሙሉ መሠዊያው ሥር አፍስሰው።+ 13 ከዚያም አንጀቱን የሸፈነውን ስብ+ ሁሉ፣ በጉበቱ ላይ ያለውን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ ውሰድ፤ በመሠዊያውም ላይ እንዲጨሱ አቃጥላቸው።+ 14 የወይፈኑን ሥጋ፣ ቆዳውንና ፈርሱን ግን ከሰፈሩ ውጭ አውጥተህ በእሳት ታቃጥለዋለህ። ይህ የኃጢአት መባ ነው።
-
-
ዘሌዋውያን 16:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 “ከዚያም አሮን ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያቅርብ፤ ለራሱም+ ሆነ ለቤቱ ያስተሰርያል።
-