ዘኁልቁ 6:23-27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤልን ሕዝብ የምትባርኩት+ በዚህ መንገድ ነው። እንዲህ በሏቸው፦ 24 “ይሖዋ ይባርክህ፤+ ደግሞም ይጠብቅህ። 25 ይሖዋ ፊቱን ያብራልህ፤+ ሞገሱንም ያሳይህ። 26 ይሖዋ ፊቱን ወደ አንተ ይመልስ፤ ሰላምም ይስጥህ።”’+ 27 እኔም እንድባርካቸው+ ስሜን በእስራኤል ሕዝብ ላይ ያድርጉ።”+ ዘዳግም 10:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “በዚያን ጊዜ ይሖዋ፣ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከም፣+ ይሖዋን ለማገልገል በፊቱ እንዲቆምና እስከ ዛሬ እንደሚያደርገው በስሙ እንዲባርክ+ የሌዊን ነገድ ለየ።+ ዘዳግም 21:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “ሌዋውያኑ ካህናት ይቅረቡ፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ እሱን እንዲያገለግሉና በይሖዋ ስም እንዲባርኩ+ የመረጠው እነሱን ነው።+ ደግሞም የኃይል ጥቃትን በተመለከተ ለሚነሳ ለማንኛውም ክርክር እልባት የሚሰጡት እነሱ ናቸው።+ 1 ዜና መዋዕል 23:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 የአምራም ወንዶች ልጆች አሮን+ እና ሙሴ+ ነበሩ። ሆኖም አሮንና ወንዶች ልጆቹ ቅድስተ ቅዱሳኑን እንዲቀድሱ፣ በይሖዋ ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ እሱን እንዲያገለግሉና ምንጊዜም በስሙ እንዲባርኩ+ በቋሚነት ተለይተው ነበር።+
23 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤልን ሕዝብ የምትባርኩት+ በዚህ መንገድ ነው። እንዲህ በሏቸው፦ 24 “ይሖዋ ይባርክህ፤+ ደግሞም ይጠብቅህ። 25 ይሖዋ ፊቱን ያብራልህ፤+ ሞገሱንም ያሳይህ። 26 ይሖዋ ፊቱን ወደ አንተ ይመልስ፤ ሰላምም ይስጥህ።”’+ 27 እኔም እንድባርካቸው+ ስሜን በእስራኤል ሕዝብ ላይ ያድርጉ።”+
8 “በዚያን ጊዜ ይሖዋ፣ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከም፣+ ይሖዋን ለማገልገል በፊቱ እንዲቆምና እስከ ዛሬ እንደሚያደርገው በስሙ እንዲባርክ+ የሌዊን ነገድ ለየ።+
5 “ሌዋውያኑ ካህናት ይቅረቡ፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ እሱን እንዲያገለግሉና በይሖዋ ስም እንዲባርኩ+ የመረጠው እነሱን ነው።+ ደግሞም የኃይል ጥቃትን በተመለከተ ለሚነሳ ለማንኛውም ክርክር እልባት የሚሰጡት እነሱ ናቸው።+
13 የአምራም ወንዶች ልጆች አሮን+ እና ሙሴ+ ነበሩ። ሆኖም አሮንና ወንዶች ልጆቹ ቅድስተ ቅዱሳኑን እንዲቀድሱ፣ በይሖዋ ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ እሱን እንዲያገለግሉና ምንጊዜም በስሙ እንዲባርኩ+ በቋሚነት ተለይተው ነበር።+