ዘዳግም 1:38 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 ወደ ምድሪቱ የሚገባው+ በፊትህ የሚቆመው የነዌ ልጅ ኢያሱ ነው።+ እስራኤላውያን ምድሪቱን እንዲወርሱ የሚያደርገው እሱ ስለሆነ አበርታው።”)*+ ዘዳግም 31:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ከፊትህ የሚሻገረው አምላክህ ይሖዋ ነው፤ እሱ ራሱም እነዚህን ብሔራት ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ አንተም ታባርራቸዋለህ።+ ልክ ይሖዋ በተናገረውም መሠረት እየመራ የሚያሻግርህ ኢያሱ ነው።+ ዘዳግም 34:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሆኖም ይሖዋ ፊት ለፊት እንዳወቀው+ እንደ ሙሴ ያለ ሌላ ነቢይ እስካሁን በእስራኤል ተነስቶ አያውቅም።+
3 ከፊትህ የሚሻገረው አምላክህ ይሖዋ ነው፤ እሱ ራሱም እነዚህን ብሔራት ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ አንተም ታባርራቸዋለህ።+ ልክ ይሖዋ በተናገረውም መሠረት እየመራ የሚያሻግርህ ኢያሱ ነው።+