ዘፍጥረት 30:17, 18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 አምላክም ሊያን ሰማት፤ መልስም ሰጣት፤ እሷም ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ አምስተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 18 ሊያም “አገልጋዬን ለባሌ ስለሰጠሁ አምላክ ደሞዜን* ከፈለኝ” አለች። በመሆኑም ስሙን ይሳኮር*+ አለችው። ዘፍጥረት 46:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 የይሳኮር ወንዶች ልጆች ቶላ፣ ፑዋ፣ ዮብ እና ሺምሮን ነበሩ።+ ዘኁልቁ 2:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ከእሱም ቀጥሎ የሚሰፍረው የይሳኮር ነገድ ይሆናል፤ የይሳኮር ልጆች አለቃ የጹአር ልጅ ናትናኤል+ ነው። 6 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 54,400 ናቸው።+
17 አምላክም ሊያን ሰማት፤ መልስም ሰጣት፤ እሷም ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ አምስተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 18 ሊያም “አገልጋዬን ለባሌ ስለሰጠሁ አምላክ ደሞዜን* ከፈለኝ” አለች። በመሆኑም ስሙን ይሳኮር*+ አለችው።