ዘፍጥረት 30:4-6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በዚህ መሠረት አገልጋይዋን ባላን ሚስት እንድትሆነው ሰጠችው፤ ያዕቆብም ከእሷ ጋር ግንኙነት ፈጸመ።+ 5 ባላም ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 6 ራሔልም “አምላክ ዳኛ ሆነልኝ፤ ቃሌንም ሰማ። በመሆኑም ወንድ ልጅ ሰጠኝ” አለች። በዚህም የተነሳ ስሙን ዳን*+ አለችው። ዘፍጥረት 46:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 የዳን+ ልጅ* ሁሺም+ ነበር። ዘኁልቁ 2:25, 26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 “ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የዳን ምድብ በየምድቡ* በመሆን በስተ ሰሜን አቅጣጫ ይስፈር፤ የዳን ልጆች አለቃ የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር+ ነው። 26 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 62,700 ናቸው።+ ዘኁልቁ 10:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ከዚያም ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የዳን ልጆች ምድብ ለሁሉም ምድቦች የኋላ ደጀን በመሆን በየምድቡ* ተነስቶ ተጓዘ፤ የሠራዊቱም አለቃ የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር+ ነበር።
4 በዚህ መሠረት አገልጋይዋን ባላን ሚስት እንድትሆነው ሰጠችው፤ ያዕቆብም ከእሷ ጋር ግንኙነት ፈጸመ።+ 5 ባላም ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 6 ራሔልም “አምላክ ዳኛ ሆነልኝ፤ ቃሌንም ሰማ። በመሆኑም ወንድ ልጅ ሰጠኝ” አለች። በዚህም የተነሳ ስሙን ዳን*+ አለችው።
25 “ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የዳን ምድብ በየምድቡ* በመሆን በስተ ሰሜን አቅጣጫ ይስፈር፤ የዳን ልጆች አለቃ የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር+ ነው። 26 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 62,700 ናቸው።+
25 ከዚያም ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የዳን ልጆች ምድብ ለሁሉም ምድቦች የኋላ ደጀን በመሆን በየምድቡ* ተነስቶ ተጓዘ፤ የሠራዊቱም አለቃ የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር+ ነበር።