ዘኁልቁ 23:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ከዚያም ባላቅ እንዲህ አለው፦ “እባክህ፣ እነሱን ማየት ወደምትችልበት ሌላ ቦታ አብረን እንሂድ። እርግጥ ሁሉንም አታያቸውም፤ የምታያቸው በከፊል ብቻ ነው። እዚያ ሆነህ እርገምልኝ።”+ 14 እሱም በጲስጋ አናት+ ላይ ወደሚገኘው የጾፊም ሜዳ ወሰደው፤ በዚያም ሰባት መሠዊያዎችን ሠርቶ በእያንዳንዱ መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረበ።+ ዘኁልቁ 23:28-30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ስለዚህ ባላቅ በለዓምን፣ የሺሞንን* ፊት ለፊት ማየት ወደሚቻልበት ወደ ፌጎር አናት ወሰደው።+ 29 ከዚያም በለዓም ባላቅን “እዚህ ቦታ ላይ ሰባት መሠዊያዎች ሥራልኝ፤ እንዲሁም ሰባት በሬዎችና ሰባት አውራ በጎች አዘጋጅልኝ” አለው።+ 30 ባላቅም በለዓም እንዳለው አደረገ፤ ከዚያም በእያንዳንዱ መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረበ።
13 ከዚያም ባላቅ እንዲህ አለው፦ “እባክህ፣ እነሱን ማየት ወደምትችልበት ሌላ ቦታ አብረን እንሂድ። እርግጥ ሁሉንም አታያቸውም፤ የምታያቸው በከፊል ብቻ ነው። እዚያ ሆነህ እርገምልኝ።”+ 14 እሱም በጲስጋ አናት+ ላይ ወደሚገኘው የጾፊም ሜዳ ወሰደው፤ በዚያም ሰባት መሠዊያዎችን ሠርቶ በእያንዳንዱ መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረበ።+
28 ስለዚህ ባላቅ በለዓምን፣ የሺሞንን* ፊት ለፊት ማየት ወደሚቻልበት ወደ ፌጎር አናት ወሰደው።+ 29 ከዚያም በለዓም ባላቅን “እዚህ ቦታ ላይ ሰባት መሠዊያዎች ሥራልኝ፤ እንዲሁም ሰባት በሬዎችና ሰባት አውራ በጎች አዘጋጅልኝ” አለው።+ 30 ባላቅም በለዓም እንዳለው አደረገ፤ ከዚያም በእያንዳንዱ መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረበ።