ዘፀአት 23:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 “በምድርህ ላይ የሚገኘውን መጀመሪያ የደረሰውን ምርጥ ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቤት አምጣ።+ “የፍየል ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል።+ ዘኁልቁ 18:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በተጨማሪም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ለእኔ በሚቀርቡት መዋጮዎች+ ላይ እኔ ራሴ ኃላፊ አድርጌ ሾሜሃለሁ። እስራኤላውያን የሚያዋጧቸውን ቅዱስ ነገሮች ሁሉ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ ድርሻችሁ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም ቋሚ ድርሻችሁ ነው።+ ዘኁልቁ 18:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “ለይሖዋ የሚሰጡትን ምርጥ የሆነውን ዘይት ሁሉ፣ ምርጥ የሆነውን አዲስ የወይን ጠጅና እህል ሁሉ ይኸውም የፍሬያቸውን በኩራት+ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።+ 2 ዜና መዋዕል 31:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በተጨማሪም ሕዝቅያስ የይሖዋን ሕግ በጥብቅ መከተል* እንዲችሉ በኢየሩሳሌም የሚኖረው ሕዝብ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ ተገቢውን ድርሻ እንዲሰጥ አዘዘ።+ ነህምያ 12:44 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 44 በዚያን ቀን መዋጮዎች፣+ የእህል በኩራትና+ አሥራት+ በሚቀመጡባቸው ግምጃ ቤቶች+ ላይ ሰዎች ተሾሙ። እነሱም በሕጉ ላይ በታዘዘው መሠረት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የሚሰጠውን ድርሻ ከየከተሞቹ እርሻዎች እየሰበሰቡ ወደዚያ ማስገባት ነበረባቸው፤+ ምክንያቱም በሚያገለግሉት ካህናትና ሌዋውያን+ የተነሳ በይሁዳ ውስጥ ታላቅ ደስታ ነበር።
8 በተጨማሪም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ለእኔ በሚቀርቡት መዋጮዎች+ ላይ እኔ ራሴ ኃላፊ አድርጌ ሾሜሃለሁ። እስራኤላውያን የሚያዋጧቸውን ቅዱስ ነገሮች ሁሉ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ ድርሻችሁ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም ቋሚ ድርሻችሁ ነው።+
44 በዚያን ቀን መዋጮዎች፣+ የእህል በኩራትና+ አሥራት+ በሚቀመጡባቸው ግምጃ ቤቶች+ ላይ ሰዎች ተሾሙ። እነሱም በሕጉ ላይ በታዘዘው መሠረት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የሚሰጠውን ድርሻ ከየከተሞቹ እርሻዎች እየሰበሰቡ ወደዚያ ማስገባት ነበረባቸው፤+ ምክንያቱም በሚያገለግሉት ካህናትና ሌዋውያን+ የተነሳ በይሁዳ ውስጥ ታላቅ ደስታ ነበር።