-
ዘዳግም 21:6-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ከዚያም የሞተው ሰው ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ የሆኑት የከተማዋ ሽማግሌዎች በሙሉ በሸለቆው ውስጥ አንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ፤+ 7 እንዲህ ብለውም ይናገሩ፦ ‘እጆቻችን ይህን ደም አላፈሰሱም፤ ዓይኖቻችንም ይህ ደም ሲፈስ አላዩም። 8 ይሖዋ ሆይ፣ የታደግከውን+ ሕዝብህን እስራኤልን በዚህ ድርጊት ተጠያቂ አታድርገው፤ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የተፈጸመ በደልም በሕዝብህ በእስራኤል መካከል እንዲኖር አትፍቀድ።’+ እነሱም በደም ዕዳው ተጠያቂ አይሆኑም። 9 በዚህ መንገድ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የተፈጸመን በደል ከመካከልህ በማስወገድ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ።
-