-
ዘዳግም 20:4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ ጠላቶቻችሁን ሊዋጋላችሁና ሊያድናችሁ አብሯችሁ ይወጣል።’+
-
-
ኢያሱ 10:11-14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 እነሱም ከእስራኤላውያን በመሸሽ የቤትሆሮንን ቁልቁለት እየወረዱ ሳሉ እስከ አዜቃ ድረስ ይሖዋ ከሰማይ ትላልቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ እነሱም ሞቱ። እንዲያውም በእስራኤላውያን ሰይፍ ከሞቱት ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት ይበልጣሉ።
12 ይሖዋ አሞራውያንን ከእስራኤላውያን ፊት ባባረረበት ዕለት ኢያሱ በእስራኤላውያን ፊት ይሖዋን እንዲህ አለው፦
“ፀሐይ ሆይ፣ በገባኦን ላይ ቁሚ፤+
አንቺም ጨረቃ ሆይ፣ በአይሎን ሸለቆ* ላይ ቀጥ በይ!”
13 በመሆኑም ብሔሩ ጠላቶቹን እስኪበቀል ድረስ ፀሐይ ባለችበት ቆመች፤ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህስ በያሻር መጽሐፍ+ ላይ ተጽፎ የሚገኝ አይደለም? ፀሐይ በሰማይ መካከል ባለችበት ቆመች፤ ለአንድ ቀን ያህል ለመጥለቅ አልቸኮለችም። 14 ይሖዋ የሰውን ቃል የሰማበት+ እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ ፈጽሞ አልነበረም፤ ምክንያቱም ይሖዋ ለእስራኤል እየተዋጋ ነበር።+
-
-
ኢያሱ 10:42አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
42 ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ነገሥታትና ምድራቸውን በሙሉ በአንድ ጊዜ ተቆጣጠረ፤ ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ለእስራኤላውያን እየተዋጋላቸው ነበር።+
-