የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ሳሙኤል 11:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 በመሆኑም ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጊልጋል ሄደ፤ በጊልጋልም ሳኦልን በይሖዋ ፊት አነገሡት። በዚያም በይሖዋ ፊት የኅብረት መሥዋዕቶችን አቀረቡ፤+ ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ እጅግ ተደሰቱ።+

  • 1 ሳሙኤል 13:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፦ “የፈጸምከው የሞኝነት ድርጊት ነው። አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን ትእዛዝ አልጠበቅክም።+ ጠብቀህ ቢሆን ኖሮ ይሖዋ መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ባጸናልህ ነበር።

  • 1 ሳሙኤል 15:26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 26 ሳሙኤል ግን ሳኦልን “አንተ የይሖዋን ቃል ስላልተቀበልክና ይሖዋም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆነህ እንድትቀጥል ስላልፈቀደ ከአንተ ጋር አልመለስም” አለው።+

  • 1 ሳሙኤል 28:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 በመጨረሻም ሳኦል አገልጋዮቹን “መናፍስት ጠሪ+ ፈልጉልኝ፤ እኔም ሄጄ ምክር እጠይቃታለሁ” አላቸው። አገልጋዮቹም “በኤንዶር+ አንዲት መናፍስት ጠሪ አለች” በማለት መለሱለት።

  • 1 ሳሙኤል 31:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 ከዚያም ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን “እነዚህ ያልተገረዙ+ ሰዎች መጥተው እንዳይወጉኝና በጭካኔ እንዳያሠቃዩኝ* ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበር ፈቃደኛ አልሆነም። በመሆኑም ሳኦል ሰይፉን ወስዶ በላዩ ላይ ወድቆ ሞተ።+

  • 2 ሳሙኤል 1:23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 23 ሳኦልና ዮናታን+ በሕይወት ሳሉ የሚወደዱና የሚደነቁ* ነበሩ፤

      ሲሞቱም አልተለያዩም።+

      ከንስር ይልቅ ፈጣኖች፣+

      ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ