-
1 ሳሙኤል 18:6-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ዳዊትና አብረውት ያሉት ሰዎች ፍልስጤማውያንን መትተው በተመለሱ ጊዜ በመላው የእስራኤል ከተሞች የሚገኙ ሴቶች አታሞና+ ባለ ሦስት አውታር መሣሪያ ይዘው በደስታ እየዘፈኑና+ እየጨፈሩ ንጉሥ ሳኦልን ለመቀበል ወጡ። 7 እየጨፈሩ የነበሩት ሴቶችም እንዲህ እያሉ ዘፈኑ፦
“ሳኦል ሺዎችን ገደለ፤
ዳዊት ደግሞ አሥር ሺዎችን ገደለ።”+
8 ሳኦልም እጅግ ተቆጣ፤+ ዘፈኑም አላስደሰተውም፤ በመሆኑም “ለዳዊት አሥር ሺህ አሉለት፤ ለእኔ ግን ሺህ ብቻ፤ ያልተሰጠው ነገር እኮ መንግሥት ብቻ ነው!” አለ።+
-