-
1 ሳሙኤል 17:50አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
50 በዚህ ሁኔታ ዳዊት ፍልስጤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው፤ ዳዊት በእጁ ሰይፍ ባይዝም ፍልስጤማዊውን መትቶ ገደለው።+
-
-
1 ሳሙኤል 18:7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 እየጨፈሩ የነበሩት ሴቶችም እንዲህ እያሉ ዘፈኑ፦
“ሳኦል ሺዎችን ገደለ፤
ዳዊት ደግሞ አሥር ሺዎችን ገደለ።”+
-
-
1 ሳሙኤል 19:8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 ከጊዜ በኋላ ሌላ ጦርነት ተነሳ፤ ዳዊትም ወጥቶ ከፍልስጤማውያን ጋር ተዋጋ፤ ክፉኛም ጨፈጨፋቸው፤ እነሱም ከፊቱ ሸሹ።
-
-
2 ሳሙኤል 10:18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 ሆኖም ሶርያውያን ከእስራኤላውያን ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን መካከል 700 ሠረገለኞችንና 40,000 ፈረሰኞችን ገደለ፤ የሠራዊታቸው አለቃ የሆነውን ሾባክንም መታው፤ እሱም እዚያው ሞተ።+
-