-
1 ነገሥት 21:19-24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 እንዲህም በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሰው ገድለህ+ ንብረቱን ወሰድክ+ አይደል?”’ ከዚያም እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ቦታ የአንተንም ደም ይልሱታል።”’”+
20 አክዓብም ኤልያስን “ጠላቴ ሆይ፣ አገኘኸኝ?” አለው፤+ እሱም እንዲህ አለው፦ “አዎ፣ አግኝቼሃለሁ። ‘እንግዲህ አንተ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ቆርጠህ ስለተነሳህ*+ 21 ጥፋት አመጣብሃለሁ፤ እየተከታተልኩም ሙልጭ አድርጌ እጠርግሃለሁ፤ እንዲሁም በእስራኤል ውስጥ የሚገኘውን ምስኪኑንና ደካማውን+ ጨምሮ የአክዓብ የሆነውን ወንድ* ሁሉ አጠፋለሁ።+ 22 ቁጣዬን ስላነሳሳህና እስራኤላውያን ኃጢአት እንዲፈጽሙ ስላደረግክ ቤትህን እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም+ ቤትና እንደ አኪያህ ልጅ እንደ ባኦስ+ ቤት አደርገዋለሁ።’ 23 ኤልዛቤልን በተመለከተም ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ ‘ውሾች በኢይዝራኤል በሚገኘው ቁራሽ መሬት ላይ ኤልዛቤልን ይበሏታል።+ 24 ከአክዓብ ወገን የሆነውን፣ በከተማ ውስጥ የሚሞተውን ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳ ላይ የሚሞተውን ደግሞ የሰማይ አሞሮች ይበሉታል።+
-
-
2 ነገሥት 9:7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 አንተም የጌታህን የአክዓብን ቤት ትመታለህ፤ እኔም የአገልጋዮቼን የነቢያትን ደምና በኤልዛቤል እጅ የሞቱትን የይሖዋን አገልጋዮች ሁሉ ደም እበቀላለሁ።+
-