2 ነገሥት 8:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ስለዚህ ንጉሥ ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከሃዛኤል ጋር በተዋጋበት ጊዜ ሶርያውያን በራማ ካቆሰሉት ቁስል ለማገገም ወደ ኢይዝራኤል+ ተመለሰ።+ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም ቆስሎ* ስለነበር እሱን ለማየት ወደ ኢይዝራኤል ወረደ። 2 ነገሥት 9:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ኢዮራምም “ሠረገላዬን አዘጋጁልኝ!” አለ። በመሆኑም የጦር ሠረገላው ተዘጋጀለት፤ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራምና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም+ በየራሳቸው የጦር ሠረገላ ሆነው ኢዩን ለመገናኘት ወጡ። በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ የእርሻ ቦታ+ ላይ ከእሱ ጋር ተገናኙ። 2 ነገሥት 9:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ+ ይህን ሲያይ በአትክልት ቤቱ በኩል ባለው መንገድ ሸሸ። (በኋላም ኢዩ እሱን እያሳደደው “እሱንም ግደሉት!” አለ። እነሱም በይብለአም+ አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ጉር ሽቅብ በሚያስወጣው መንገድ ላይ ሠረገላው ውስጥ እንዳለ አቆሰሉት። እሱ ግን ወደ መጊዶ ሸሸ፤ በዚያም ሞተ። 2 ዜና መዋዕል 22:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ከዚያም የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የመጨረሻ ልጁን አካዝያስን* በእሱ ምትክ አነገሡት፤ ከዓረቦቹ ጋር ወደ ሰፈሩ የመጡት ወራሪዎች ታላላቆቹን በሙሉ ገድለዋቸው ነበር።+ በመሆኑም የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ።+
29 ስለዚህ ንጉሥ ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከሃዛኤል ጋር በተዋጋበት ጊዜ ሶርያውያን በራማ ካቆሰሉት ቁስል ለማገገም ወደ ኢይዝራኤል+ ተመለሰ።+ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም ቆስሎ* ስለነበር እሱን ለማየት ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።
21 ኢዮራምም “ሠረገላዬን አዘጋጁልኝ!” አለ። በመሆኑም የጦር ሠረገላው ተዘጋጀለት፤ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራምና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም+ በየራሳቸው የጦር ሠረገላ ሆነው ኢዩን ለመገናኘት ወጡ። በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ የእርሻ ቦታ+ ላይ ከእሱ ጋር ተገናኙ።
27 የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ+ ይህን ሲያይ በአትክልት ቤቱ በኩል ባለው መንገድ ሸሸ። (በኋላም ኢዩ እሱን እያሳደደው “እሱንም ግደሉት!” አለ። እነሱም በይብለአም+ አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ጉር ሽቅብ በሚያስወጣው መንገድ ላይ ሠረገላው ውስጥ እንዳለ አቆሰሉት። እሱ ግን ወደ መጊዶ ሸሸ፤ በዚያም ሞተ።
22 ከዚያም የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የመጨረሻ ልጁን አካዝያስን* በእሱ ምትክ አነገሡት፤ ከዓረቦቹ ጋር ወደ ሰፈሩ የመጡት ወራሪዎች ታላላቆቹን በሙሉ ገድለዋቸው ነበር።+ በመሆኑም የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ።+