-
ኢያሱ 21:27-33አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 የሌዋውያን ቤተሰቦች የሆኑት ጌድሶናውያንም+ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ የሆነችውን በባሳን የምትገኘውን ጎላንን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም በኤሽተራን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም ሁለት ከተሞችን ወሰዱ።
28 ከይሳኮር ነገድ+ ላይ ቂሾንን ከነግጦሽ መሬቷ፣ ዳብራትን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ 29 ያርሙትን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ኤንጋኒምን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጡ።
30 ከአሴር ነገድ+ ላይ ሚሽአልን ከነግጦሽ መሬቷ፣ አብዶንን ከነግጦሽ መሬቷ፣ 31 ሄልቃትን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ሬሆብን+ ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጡ።
32 ከንፍታሌም ነገድ ላይ ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ+ የሆነችውን በገሊላ የምትገኘውን ቃዴሽን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ሃሞትዶርን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ቃርታንን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም ሦስት ከተሞችን ሰጡ።
33 የጌድሶናውያን ከተሞች በየቤተሰባቸው በአጠቃላይ 13 ከተሞች ከነግጦሽ መሬቶቻቸው ነበሩ።
-