-
1 ሳሙኤል 31:1-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
31 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል ጋር እየተዋጉ ነበር።+ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጤማውያን ፊት ሸሹ፤ ብዙዎቹም በጊልቦአ+ ተራራ ላይ ተገደሉ። 2 ፍልስጤማውያንም ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን እግር በእግር ተከታተሏቸው፤ ፍልስጤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንን፣+ አቢናዳብንና ሜልኪሳን መትተው ገደሏቸው።+ 3 ውጊያው በሳኦል ላይ በረታ፤ ቀስተኞቹም አገኙት፤ እነሱም ክፉኛ አቆሰሉት።+ 4 ከዚያም ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን “እነዚህ ያልተገረዙ+ ሰዎች መጥተው እንዳይወጉኝና በጭካኔ እንዳያሠቃዩኝ* ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበር ፈቃደኛ አልሆነም። በመሆኑም ሳኦል ሰይፉን ወስዶ በላዩ ላይ ወድቆ ሞተ።+ 5 ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል መሞቱን ሲያይ+ እሱም በራሱ ሰይፍ ላይ ወድቆ ከእሱ ጋር ሞተ።
-
-
2 ሳሙኤል 1:25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 ኃያላኑ በጦርነት ላይ እንዴት እንዲህ ይውደቁ!
ዮናታን በኮረብቶችህ ላይ ተገድሎ ተጋድሟል!+
-