-
1 ዜና መዋዕል 10:1-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 ፍልስጤማውያንም ከእስራኤል ጋር እየተዋጉ ነበር። የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጤማውያን ፊት ሸሹ፤ ብዙዎቹም በጊልቦአ ተራራ ላይ ተገደሉ።+ 2 ፍልስጤማውያን ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን እግር በእግር ተከታተሏቸው፤ ፍልስጤማውያንም የሳኦልን ወንዶች ልጆች ዮናታንን፣ አቢናዳብንና ሜልኪሳን+ መተው ገደሏቸው። 3 ውጊያው በሳኦል ላይ በረታ፤ ቀስተኞቹም አገኙት፤ ደግሞም አቆሰሉት።+ 4 ከዚያም ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን “እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች መጥተው በጭካኔ እንዳያሠቃዩኝ*+ ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበር ፈቃደኛ አልሆነም። በመሆኑም ሳኦል ሰይፉን ወስዶ በላዩ ላይ ወድቆ ሞተ።+ 5 ጋሻ ጃግሬው ሳኦል መሞቱን ሲያይ እሱም በራሱ ሰይፍ ላይ ወድቆ ሞተ።
-