-
2 ነገሥት 22:3-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ንጉሥ ኢዮስያስ፣ በነገሠ በ18ኛው ዓመት የመሹላም ልጅ፣ የአዜልያ ልጅ የሆነውን ጸሐፊውን ሳፋንን እንዲህ ሲል ወደ ይሖዋ ቤት ላከው፦+ 4 “ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኬልቅያስ+ ሂድ፤ በር ጠባቂዎቹ ከሕዝቡ ላይ የሰበሰቡትንና ወደ ይሖዋ ቤት የገባውን ገንዘብ በአጠቃላይ እንዲሰበስብ አድርግ።+ 5 ገንዘቡን በይሖዋ ቤት የሚከናወነውን ሥራ እንዲቆጣጠሩ ለተሾሙት ሰዎች ይስጧቸው፤ እነሱ ደግሞ በይሖዋ ቤት ውስጥ የፈረሰውን* ለሚጠግኑት ሠራተኞች ይስጡ፤+ 6 ይኸውም ለእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹ፣ ለግንባታ ባለሙያዎቹና ለግንበኞቹ ያስረክቡ፤ እነሱም ገንዘቡን ለቤቱ ጥገና የሚያስፈልጉትን ሳንቃዎችና ጥርብ ድንጋዮች ለመግዛት ይጠቀሙበታል።+
-