ዘሌዋውያን 23:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘በዚህ በሰባተኛው ወር ከ15ኛው ቀን ጀምሮ ለሰባት ቀን ያህል ለይሖዋ የዳስ* በዓል ይከበራል።+ ዘዳግም 16:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 “እህልህን ከአውድማህ፣ ዘይትህንና የወይን ጠጅህን ከመጭመቂያህ በምታስገባበት ጊዜ የዳስ* በዓልን+ ለሰባት ቀን አክብር።