-
ዘኁልቁ 29:12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 “‘በሰባተኛው ወር በ15ኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ፤ ለሰባት ቀንም ለይሖዋ በዓል አክብሩ።+
-
-
ነህምያ 8:14-18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ከዚያም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት ባዘዘው ሕግ ውስጥ እስራኤላውያን በሰባተኛው ወር በሚከበረው በዓል ወቅት ዳስ*+ ውስጥ መቀመጥ እንዳለባቸው የሚገልጽ ሐሳብ ተጽፎ አገኙ፤ 15 እንዲሁም “ወደ ተራራማው አካባቢ ውጡና በተጻፈው መሠረት ዳሶችን ለመሥራት ከወይራ ዛፍ፣ ከዘይት ዛፍ፣ ከአደስ ዛፍ፣ ከዘንባባና ከሌሎች ዛፎች ቅጠል ያላቸውን ቅርንጫፎች አምጡ” የሚል አዋጅ በከተሞቻቸው በሙሉና በመላው ኢየሩሳሌም ማወጅ እንዳለባቸው+ የሚገልጽ ሐሳብ ተጽፎ አገኙ።
16 ስለዚህ ሕዝቡ ወጥቶ እነዚህን ቅጠሎች በማምጣት እያንዳንዱ ሰው በቤቱ ጣሪያ ላይ እንዲሁም በግቢውና በእውነተኛው አምላክ ቤት ግቢ ውስጥ፣+ በውኃ በር+ አደባባይና በኤፍሬም በር+ አደባባይ ለራሱ ዳሶች ሠራ። 17 በዚህም መንገድ ከምርኮ የተመለሱትን ሰዎች ያቀፈው መላው ጉባኤ ዳሶችን ሠራ፤ በዳሶቹም ውስጥ ተቀመጠ፤ እስራኤላውያን ከነዌ ልጅ ከኢያሱ+ ዘመን ጀምሮ እስከዚያ ቀን ድረስ በዓሉን በዚህ መንገድ አክብረው አያውቁም ነበር፤ ስለሆነም ደስታቸው ታላቅ ሆነ።+ 18 የእውነተኛው አምላክ ሕግ+ መጽሐፍም ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ በየዕለቱ ይነበብ ነበር። እነሱም በዓሉን ለሰባት ቀን አከበሩ፤ በደንቡ መሠረትም በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ተደረገ።+
-
-
ዮሐንስ 7:2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 ይሁን እንጂ የአይሁዳውያን በዓል የሆነው የዳስ በዓል+ ተቃርቦ ነበር።
-