የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 23:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 በተጨማሪም በእርሻህ ላይ በዘራኸው መጀመሪያ በሚደርሰው የድካምህ ፍሬ የመከርን በዓል* አክብር፤+ ከእርሻህ ላይ የድካምህን ፍሬ በምትሰበስብበት በዓመቱ ማብቂያ ላይ የአዝመራ መክተቻን በዓል* አክብር።+

  • ዘሌዋውያን 23:34-36
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 34 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘በዚህ በሰባተኛው ወር ከ15ኛው ቀን ጀምሮ ለሰባት ቀን ያህል ለይሖዋ የዳስ* በዓል ይከበራል።+ 35 በመጀመሪያው ቀን ላይ ቅዱስ ጉባኤ ይሆናል፤ እናንተም ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። 36 ለሰባት ቀን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ማቅረብ ይኖርባችኋል። በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ታከብራላችሁ፤+ ለይሖዋም በእሳት የሚቀርብ መባ ማቅረብ አለባችሁ። ይህ የተቀደሰ ጉባኤ ነው። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ።

  • ዘዳግም 16:13-15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 “እህልህን ከአውድማህ፣ ዘይትህንና የወይን ጠጅህን ከመጭመቂያህ በምታስገባበት ጊዜ የዳስ* በዓልን+ ለሰባት ቀን አክብር። 14 በዓልህን በምታከብርበት ወቅት ደስ ይበልህ፤+ አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖር ሌዋዊ፣ የባዕድ አገር ሰው፣ አባት የሌለው ልጅና መበለቲቱ ደስ ይበላችሁ። 15 አምላክህ ይሖዋ ምርትህንና የእጅህን ሥራ ሁሉ ስለሚባርክልህ+ ይሖዋ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለይሖዋ ሰባት ቀን በዓሉን ታከብራለህ፤+ አንተም እጅግ ትደሰታለህ።+

  • ነህምያ 8:14-18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ከዚያም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት ባዘዘው ሕግ ውስጥ እስራኤላውያን በሰባተኛው ወር በሚከበረው በዓል ወቅት ዳስ*+ ውስጥ መቀመጥ እንዳለባቸው የሚገልጽ ሐሳብ ተጽፎ አገኙ፤ 15 እንዲሁም “ወደ ተራራማው አካባቢ ውጡና በተጻፈው መሠረት ዳሶችን ለመሥራት ከወይራ ዛፍ፣ ከዘይት ዛፍ፣ ከአደስ ዛፍ፣ ከዘንባባና ከሌሎች ዛፎች ቅጠል ያላቸውን ቅርንጫፎች አምጡ” የሚል አዋጅ በከተሞቻቸው በሙሉና በመላው ኢየሩሳሌም ማወጅ እንዳለባቸው+ የሚገልጽ ሐሳብ ተጽፎ አገኙ።

      16 ስለዚህ ሕዝቡ ወጥቶ እነዚህን ቅጠሎች በማምጣት እያንዳንዱ ሰው በቤቱ ጣሪያ ላይ እንዲሁም በግቢውና በእውነተኛው አምላክ ቤት ግቢ ውስጥ፣+ በውኃ በር+ አደባባይና በኤፍሬም በር+ አደባባይ ለራሱ ዳሶች ሠራ። 17 በዚህም መንገድ ከምርኮ የተመለሱትን ሰዎች ያቀፈው መላው ጉባኤ ዳሶችን ሠራ፤ በዳሶቹም ውስጥ ተቀመጠ፤ እስራኤላውያን ከነዌ ልጅ ከኢያሱ+ ዘመን ጀምሮ እስከዚያ ቀን ድረስ በዓሉን በዚህ መንገድ አክብረው አያውቁም ነበር፤ ስለሆነም ደስታቸው ታላቅ ሆነ።+ 18 የእውነተኛው አምላክ ሕግ+ መጽሐፍም ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ በየዕለቱ ይነበብ ነበር። እነሱም በዓሉን ለሰባት ቀን አከበሩ፤ በደንቡ መሠረትም በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ተደረገ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ