20 ጠባቂውም “መልእክተኛው እነሱ ጋ ደርሷል፤ ሆኖም አልተመለሰም፤ ሰውየው ሠረገላ አነዳዱ የኒምሺን የልጅ ልጅ የኢዩን ይመስላል፤ የሚነዳው ልክ እንደ እብድ ነውና” በማለት ተናገረ። 21 ኢዮራምም “ሠረገላዬን አዘጋጁልኝ!” አለ። በመሆኑም የጦር ሠረገላው ተዘጋጀለት፤ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራምና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም+ በየራሳቸው የጦር ሠረገላ ሆነው ኢዩን ለመገናኘት ወጡ። በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ የእርሻ ቦታ+ ላይ ከእሱ ጋር ተገናኙ።