የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 25:13-15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ከለዳውያኑም የይሖዋን ቤት የመዳብ ዓምዶች+ እንዲሁም በይሖዋ ቤት ውስጥ የነበሩትን የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎችና+ የመዳብ ባሕር+ ሰባብረው መዳቡን ወደ ባቢሎን አጋዙ።+ 14 በተጨማሪም አመድ ማጠራቀሚያዎቹን፣ አካፋዎቹን፣ የእሳት ማጥፊያዎቹን፣ ጽዋዎቹንና ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉትን የመዳብ ዕቃዎች ሁሉ ወሰዱ። 15 የዘቦቹ አለቃ ከንጹሕ ወርቅና ብር የተሠሩትን መኮስተሪያዎችና ጎድጓዳ ሳህኖች ወሰደ።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ናቡከደነጾርም በይሖዋ ቤት ያሉ የተወሰኑ ዕቃዎችን ወደ ባቢሎን ወስዶ በባቢሎን በሚገኘው ቤተ መንግሥቱ አስቀመጣቸው።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 በእውነተኛው አምላክ ቤት የነበሩትን ትላልቅም ሆኑ ትናንሽ ዕቃዎች በሙሉ፣ የይሖዋን ቤት ውድ ሀብት እንዲሁም የንጉሡንና የመኳንንቱን ውድ ሀብት ሁሉ ወደ ባቢሎን አጋዘ።+

  • ዳንኤል 1:1, 2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 1 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ከበባት።+ 2 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይሖዋ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮዓቄምንና በእውነተኛው አምላክ ቤት* ውስጥ ካሉት ዕቃዎች መካከል የተወሰኑትን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤+ እሱም በሰናኦር+ ምድር* ወደሚገኘው ወደ አምላኩ ቤት* አመጣቸው። ዕቃዎቹን በአምላኩ ግምጃ ቤት ውስጥ አስቀመጣቸው።+

  • ዳንኤል 5:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 ቤልሻዛር የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሞቅ ሲለው አባቱ ናቡከደነጾር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ የወሰዳቸውን የወርቅና የብር ዕቃዎች፣+ ንጉሡና መኳንንቱ እንዲሁም ቁባቶቹና ቅምጦቹ ይጠጡባቸው ዘንድ እንዲያመጧቸው አዘዘ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ