ነህምያ 2:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሆሮናዊው ሳንባላጥና+ አሞናዊው+ ባለሥልጣን* ጦብያ+ ይህን ነገር ሲሰሙ ለእስራኤላውያን መልካም ነገር የሚያደርግ ሰው በመምጣቱ በጣም ተበሳጩ። ነህምያ 6:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ሳንባላጥ፣ ጦብያ፣+ የዓረብ+ ተወላጅ የሆነው ጌሼምና የቀሩት ጠላቶቻችን ቅጥሩን መልሼ እንደገነባሁና+ ክፍተቶቹ ሁሉ እንደተደፈኑ ሲነገራቸው (ምንም እንኳ ገና መዝጊያዎቹን በበሮቹ ላይ ባልገጥማቸውም)፣+ 2 ሳንባላጥና ጌሼም “እስቲ መጥተህ በኦኖ+ ሸለቋማ ሜዳ ከሚገኙት መንደሮች በአንዱ ለመገናኘት ቀጠሮ እንያዝ” የሚል መልእክት ወዲያውኑ ላኩብኝ። ሆኖም እኔን ለመጉዳት አሲረው ነበር። ነህምያ 13:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ከሊቀ ካህናቱ ከኤልያሺብ+ ልጅ ከዮያዳ+ ወንዶች ልጆች መካከል አንዱ የሆሮናዊው የሳንባላጥ+ አማች ሆኖ ነበር። በመሆኑም ከአጠገቤ አባረርኩት።
6 ሳንባላጥ፣ ጦብያ፣+ የዓረብ+ ተወላጅ የሆነው ጌሼምና የቀሩት ጠላቶቻችን ቅጥሩን መልሼ እንደገነባሁና+ ክፍተቶቹ ሁሉ እንደተደፈኑ ሲነገራቸው (ምንም እንኳ ገና መዝጊያዎቹን በበሮቹ ላይ ባልገጥማቸውም)፣+ 2 ሳንባላጥና ጌሼም “እስቲ መጥተህ በኦኖ+ ሸለቋማ ሜዳ ከሚገኙት መንደሮች በአንዱ ለመገናኘት ቀጠሮ እንያዝ” የሚል መልእክት ወዲያውኑ ላኩብኝ። ሆኖም እኔን ለመጉዳት አሲረው ነበር።