-
ምሳሌ 14:16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 ጥበበኛ ሰው ጠንቃቃ ነው፤ ከክፉም ይርቃል፤
ሞኝ ግን ደንታ ቢስ ነው፤* ደግሞም ከልክ በላይ በራሱ ይመካል።
-
-
ዳንኤል 5:18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 ንጉሥ ሆይ፣ ልዑሉ አምላክ ለአባትህ ለናቡከደነጾር መንግሥት፣ ታላቅነት፣ ክብርና ግርማ ሰጠው።+
-
-
ዳንኤል 5:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ሆኖም ልቡ ታብዮና አንገተ ደንዳና ሆኖ የእብሪተኝነት መንፈስ ባሳየ ጊዜ+ ከመንግሥቱ ዙፋን እንዲወርድ ተደረገ፤ ክብሩንም ተገፈፈ።
-
-
ሮም 2:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 እንግዲህ በግትርነትህና ንስሐ በማይገባው ልብህ የተነሳ በራስህ ላይ ቁጣ ታከማቻለህ። ይህ ቁጣ አምላክ የጽድቅ ፍርድ በሚፈርድበት ቀን ይገለጣል።+
-