መዝሙር 49:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 የሞኞች መንገድ ይህ ነው፤+እነሱ በሚናገሩት ከንቱ ቃል ተደስተው የሚከተሏቸው ሰዎች መንገድም ይኸው ነው። (ሴላ) 14 ለእርድ እንደሚነዱ በጎች ወደ መቃብር* እንዲወርዱ ተፈርዶባቸዋል። ሞት እረኛቸው ይሆናል፤በማለዳ ቅኖች ይገዟቸዋል።+ ደብዛቸው ይጠፋል፤+በቤተ መንግሥት ፋንታ መቃብር* መኖሪያቸው ይሆናል።+ መዝሙር 55:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ጥፋት በድንገት ይምጣባቸው!+ በሕይወት ሳሉ ወደ መቃብር* ይውረዱ፤ክፋት በመካከላቸውና በውስጣቸው ያድራልና። ሉቃስ 12:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን* ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው።+
13 የሞኞች መንገድ ይህ ነው፤+እነሱ በሚናገሩት ከንቱ ቃል ተደስተው የሚከተሏቸው ሰዎች መንገድም ይኸው ነው። (ሴላ) 14 ለእርድ እንደሚነዱ በጎች ወደ መቃብር* እንዲወርዱ ተፈርዶባቸዋል። ሞት እረኛቸው ይሆናል፤በማለዳ ቅኖች ይገዟቸዋል።+ ደብዛቸው ይጠፋል፤+በቤተ መንግሥት ፋንታ መቃብር* መኖሪያቸው ይሆናል።+