መዝሙር 5:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 የሚሉት ነገር ሁሉ ሊታመን አይችልም፤ውስጣቸው በተንኮል የተሞላ ነው።ጉሮሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤በምላሳቸው ይሸነግላሉ።*+ መዝሙር 28:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ከክፉዎችና መጥፎ ነገር ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ጎትተህ አትውሰደኝ፤+እነሱ በልባቸው ክፋት እያለ ከባልንጀሮቻቸው ጋር የሰላም ቃል የሚያወሩ ናቸው።+ መዝሙር 55:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 የሚናገራቸው ቃላት ከቅቤ ይልቅ የለሰለሱ ናቸው፤+በልቡ ውስጥ ግን ጠብ አለ። ቃሎቹ ከዘይት ይልቅ የለሰለሱ ቢሆኑምእንደተመዘዘ ሰይፍ ናቸው።+