-
መዝሙር 105:27-36አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 እነሱም ምልክቶቹን በመካከላቸው፣
ተአምራቱን በካም ምድር አደረጉ።+
28 ጨለማን ላከ፤ ምድሪቱም ጨለመች፤+
እነሱ በቃሉ ላይ አላመፁም።
29 ውኃዎቻቸውን ወደ ደም ለወጠ፤
ዓሣዎቻቸውንም ገደለ።+
31 ተናካሽ ዝንቦች እንዲወሯቸው፣
ትንኞችም በግዛቶቻቸው ሁሉ እንዲርመሰመሱ አዘዘ።+
33 ወይናቸውንና የበለስ ዛፋቸውን መታ፤
በግዛታቸው ውስጥ ያሉትንም ዛፎች አወደመ።
34 አንበጦች፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኩብኩባዎችም
እንዲወሯቸው አዘዘ።+
35 እነሱ በአገሪቱ የሚገኘውን አትክልት ሁሉ በሉ፤
የምድሪቱንም ምርት ፈጁ።
-