-
መዝሙር 78:43-51አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
43 በግብፅ አስደናቂ ምልክቶችን፣
በጾዓን ምድርም ተአምራቱን እንዴት እንዳሳየ አላሰቡም፤+
44 እንዲሁም ከጅረቶቻቸው መጠጣት እንዳይችሉ
የአባይን የመስኖ ቦዮች እንዴት ወደ ደም እንደለወጠ ዘነጉ።+
46 ሰብላቸውን ለማይጠግብ አንበጣ፣
የድካማቸውን ፍሬ ለአንበጣ መንጋ ሰጠ።+
47 የወይን ተክላቸውን በበረዶ፣
የሾላ ዛፎቻቸውንም በበረዶ ድንጋይ አጠፋ።+
49 የሚነድ ቁጣውን፣
ንዴቱን፣ መዓቱንና መቅሰፍቱን
እንዲሁም ጥፋት የሚያመጡ የመላእክት ሠራዊትን ላከባቸው።
50 ለቁጣው መንገድ ጠረገ።
ከሞት አላተረፋቸውም፤*
ለቸነፈርም አሳልፎ ሰጣቸው።
51 በመጨረሻም የግብፅን በኩሮች በሙሉ፣
በካም ድንኳኖች ውስጥ ከሚገኙትም መካከል የፍሬያቸው መጀመሪያ የሆኑትን መታ።+
-