ዘዳግም 31:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተ መሞትህ ነው፤* ይህም ሕዝብ በሚሄድበት ምድር በዙሪያው ካሉ ባዕዳን አማልክት ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ይፈጽማል።+ እኔንም ይተዉኛል፤+ ከእነሱም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ።+ ዘዳግም 32:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የሹሩን* ሲወፍር በዓመፀኝነት ተራገጠ። ሰባህ፤ ፈረጠምክ፤ ደለብክ።+ ስለሆነም የሠራውን አምላክ ተወ፤+አዳኝ የሆነለትን ዓለት ናቀ። መሳፍንት 2:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በመሆኑም እስራኤላውያን በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤ ባአልንም አገለገሉ።* + 2 ሳሙኤል 20:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 በዚህ ጊዜ የቢንያማዊው የቢክሪ ልጅ የሆነ ሳባ+ የሚባል አንድ አስቸጋሪ ሰው ነበር። እሱም ቀንደ መለከት በመንፋት+ “እኛ ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ጋር ምንም ውርሻ የለንም።+ እስራኤል ሆይ፣ እያንዳንድህ ወደ አማልክትህ* ተመለስ!” አለ።+ ነህምያ 9:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 “ይሁንና ለመታዘዝ እንቢተኞች በመሆን በአንተ ላይ ዓመፁ፤+ ለሕግህም ጀርባቸውን ሰጡ።* ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩትን ነቢያትህን ገደሉ፤ ከፍተኛ ንቀት የሚንጸባረቅባቸውንም ተግባሮች ፈጸሙ።+
16 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተ መሞትህ ነው፤* ይህም ሕዝብ በሚሄድበት ምድር በዙሪያው ካሉ ባዕዳን አማልክት ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ይፈጽማል።+ እኔንም ይተዉኛል፤+ ከእነሱም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ።+
20 በዚህ ጊዜ የቢንያማዊው የቢክሪ ልጅ የሆነ ሳባ+ የሚባል አንድ አስቸጋሪ ሰው ነበር። እሱም ቀንደ መለከት በመንፋት+ “እኛ ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ጋር ምንም ውርሻ የለንም።+ እስራኤል ሆይ፣ እያንዳንድህ ወደ አማልክትህ* ተመለስ!” አለ።+
26 “ይሁንና ለመታዘዝ እንቢተኞች በመሆን በአንተ ላይ ዓመፁ፤+ ለሕግህም ጀርባቸውን ሰጡ።* ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩትን ነቢያትህን ገደሉ፤ ከፍተኛ ንቀት የሚንጸባረቅባቸውንም ተግባሮች ፈጸሙ።+