ዘሌዋውያን 16:21, 22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ከዚያም አሮን ሁለቱንም እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ በመጫን እስራኤላውያን የሠሩትን ስህተት ሁሉ፣ መተላለፋቸውን ሁሉና ኃጢአታቸውን ሁሉ ይናዘዝበታል፤ እነዚህንም በፍየሉ ራስ ላይ ያደርጋል፤+ ፍየሉንም ለዚህ በተመደበው* ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል። 22 ፍየሉም ስህተቶቻቸውን በሙሉ ተሸክሞ+ ወደ በረሃ ይሄዳል፤+ እሱም ፍየሉን ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል።+ ኢሳይያስ 43:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ስለ ራሴ ስል+ በደልህን* እኔ ራሴ እደመስሰዋለሁ፤+ኃጢአትህንም አላስታውስም።+ ኤርምያስ 31:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 “እነሱም እያንዳንዳቸው ባልንጀራቸውን፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን ‘ይሖዋን እወቅ!’ ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም፤+ ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና”+ ይላል ይሖዋ። “በደላቸውን ይቅር እላለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስታውስም።”+
21 ከዚያም አሮን ሁለቱንም እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ በመጫን እስራኤላውያን የሠሩትን ስህተት ሁሉ፣ መተላለፋቸውን ሁሉና ኃጢአታቸውን ሁሉ ይናዘዝበታል፤ እነዚህንም በፍየሉ ራስ ላይ ያደርጋል፤+ ፍየሉንም ለዚህ በተመደበው* ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል። 22 ፍየሉም ስህተቶቻቸውን በሙሉ ተሸክሞ+ ወደ በረሃ ይሄዳል፤+ እሱም ፍየሉን ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል።+
34 “እነሱም እያንዳንዳቸው ባልንጀራቸውን፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን ‘ይሖዋን እወቅ!’ ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም፤+ ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና”+ ይላል ይሖዋ። “በደላቸውን ይቅር እላለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስታውስም።”+