8 ምድርም ወዲያና ወዲህ ትናወጥና ትንቀጠቀጥ ጀመር፤+
የሰማያት መሠረቶች ተንቀጠቀጡ፤+
እሱ ስለተቆጣም ራዱ።+
9 ከአፍንጫው ጭስ ወጣ፤
የሚባላም እሳት ከአፉ ወጣ፤+
ፍምም ከእሱ ፈለቀ።
10 ወደ ታች ሲወርድ ሰማያት እንዲያጎነብሱ አደረገ፤+
ከእግሮቹም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበር።+
11 በኪሩብ ላይ ተቀምጦ+ እየበረረ መጣ።
በመንፈስ ክንፎችም ላይ ሆኖ ይታይ ነበር።+
12 ከዚያም ጨለማን በዙሪያው እንደ መጠለያ አደረገ፣+
ጨለማውም ጥቁር ውኃና ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረው።
13 በፊቱ ካለው ብርሃን ፍም ፈለቀ።
14 ከዚያም ይሖዋ ከሰማይ ያንጎደጉድ ጀመር፤+
ልዑሉ አምላክ ድምፁን አሰማ።+
15 ፍላጻዎቹን+ አስፈንጥሮ በታተናቸው፤
መብረቁን አብርቆ ግራ አጋባቸው።+
16 በይሖዋ ተግሣጽ፣ ከአፍንጫውም በሚወጣው ኃይለኛ እስትንፋስ+
የባሕር ወለሎች ታዩ፤+
የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።