የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 28:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

      “እነሆ፣ በጽዮን የመሠረት ድንጋይ ይኸውም የተፈተነ ድንጋይ፣+

      አስተማማኝ መሠረት+ ሆኖ የተጣለ ክቡር የማዕዘን ድንጋይ+ አኖራለሁ።

      በእሱ የሚያምን አይደናገጥም።+

  • ሉቃስ 20:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ኢየሱስም እነሱን ትኩር ብሎ በመመልከት እንዲህ አለ፦ “ታዲያ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እሱ የማዕዘን ራስ ድንጋይ* ሆነ’+ ተብሎ የተጻፈው ትርጉሙ ምንድን ነው?

  • የሐዋርያት ሥራ 4:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ‘እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፣ የማዕዘን ራስ የሆነው ድንጋይ’ እሱ ነው።+

  • 1 ቆሮንቶስ 3:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ማንም ሰው ከተጣለው መሠረት ሌላ አዲስ መሠረት መጣል አይችልምና፤ ይህም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።+

  • ኤፌሶን 2:19, 20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 ስለዚህ እናንተ ከዚህ በኋላ እንግዶችና ባዕዳን አይደላችሁም፤+ ከዚህ ይልቅ ከቅዱሳን ጋር የአንድ አገር ዜጎችና+ የአምላክ ቤተሰብ አባላት ናችሁ፤+ 20 እንዲሁም በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ተገንብታችኋል፤+ ዋናው የመሠረት ድንጋይ* ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው።+

  • 1 ጴጥሮስ 2:4-7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 በሰዎች ወደተናቀው+ በአምላክ ግን ወደተመረጠውና በፊቱ ክቡር ወደሆነው ወደ እሱ ይኸውም ሕያው ወደሆነው ድንጋይ+ በመምጣት 5 እናንተ ራሳችሁ ቅዱሳን ካህናት ለመሆን እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ለመሆን እየተገነባችሁ ነው፤+ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መንፈሳዊ መሥዋዕት ማቅረብ ትችሉ ዘንድ ነው።+ 6 ምክንያቱም ቅዱስ መጽሐፉ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በጽዮን የተመረጠ ድንጋይ ይኸውም ክቡር የሆነ የማዕዘን የመሠረት ድንጋይ አኖራለሁ፤ ደግሞም በእሱ የሚያምን ሁሉ ፈጽሞ አያፍርም።”+

      7 በመሆኑም እናንተ አማኞች ስለሆናችሁ እሱ ለእናንተ ክቡር ነው፤ የማያምኑትን በተመለከተ ግን እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፦ “ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣+ እሱ የማዕዘን ራስ ድንጋይ* ሆነ”፤+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ