-
ዘፍጥረት 1:9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 በመቀጠልም አምላክ “ከሰማያት በታች ያሉት ውኃዎች አንድ ቦታ ላይ ይሰብሰቡና ደረቁ መሬት ይገለጥ” አለ።+ እንዳለውም ሆነ።
-
-
ኢዮብ 38:11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ደግሞም ‘እስከዚህ ድረስ መምጣት ትችላለህ፤ ከዚህ ግን አታልፍም፤
የኩሩው ማዕበልህም ገደብ ይህ ነው’ ባልኩ ጊዜ+ አንተ የት ነበርክ?
-
-
መዝሙር 136:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ምድርን በውኃዎች ላይ ዘረጋ፤+
ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።
-
-
ኤርምያስ 5:22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 ‘እኔን አትፈሩም?’ ይላል ይሖዋ፤
‘በፊቴስ ልትሸበሩ አይገባም?
ውኃው አልፎ እንዳይሄድ፣ በማይሻር ድንጋጌ
አሸዋውን የባሕሩ ወሰን አድርጌ የሠራሁት እኔ ነኝ።
ሞገዶቹ ቢናወጡም ጥሰው መሄድ አይችሉም፤
ቢያስገመግሙም ከዚያ አልፈው መሄድ አይችሉም።+
-