መዝሙር 115:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ሙታንም ሆኑ ወደ ዝምታው ዓለም* የሚወርዱ ሁሉ፣+ያህን አያወድሱም።+ መዝሙር 146:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በመኳንንትም* ሆነማዳን በማይችሉ ሰዎች አትታመኑ።+ 4 መንፈሱ* ትወጣለች፤ ወደ መሬት ይመለሳል፤+በዚያው ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል።+ ኢሳይያስ 38:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 መቃብር* ከፍ ከፍ ሊያደርግህ አይችልምና፤+ሞትም ሊያወድስህ አይችልም።+ ወደ ጉድጓድ የሚወርዱ በታማኝነትህ ተስፋ ሊያደርጉ አይችሉም።+