የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ሳሙኤል 13:12, 13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 በመሆኑም ‘እንግዲህ ፍልስጤማውያን ወደ ጊልጋል ወርደው ሊወጉኝ ነው፤ እኔ ደግሞ ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳየኝ አለመንኩም’ ብዬ አሰብኩ። ስለሆነም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ።”

      13 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፦ “የፈጸምከው የሞኝነት ድርጊት ነው። አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን ትእዛዝ አልጠበቅክም።+ ጠብቀህ ቢሆን ኖሮ ይሖዋ መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ባጸናልህ ነበር።

  • 1 ሳሙኤል 15:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 ከዚያም ሳሙኤል እንዲህ አለ፦ “ይሖዋን ይበልጥ የሚያስደስተው የትኛው ነው? የሚቃጠሉ መባዎችንና መሥዋዕቶችን+ ማቅረብ ወይስ የይሖዋን ቃል መታዘዝ? እነሆ፣ መታዘዝ ከመሥዋዕት፣+ መስማትም ከአውራ በግ ስብ+ ይበልጣል፤

  • ምሳሌ 21:27
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 27 የክፉ ሰው መሥዋዕት አስጸያፊ ነው።+

      በክፉ ዓላማ ተነሳስቶ* ሲያቀርብማ ምንኛ የከፋ ይሆናል!

  • ኢሳይያስ 1:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ከንቱ የሆኑትን የእህል መባዎች ከዚህ በኋላ አታምጡ።

      ዕጣናችሁ በፊቴ አስጸያፊ ነው።+

      የአዲስ ጨረቃ+ በዓልንና ሰንበትን+ ታከብራላችሁ፤ ስብሰባም+ ትጠራላችሁ።

      በአንድ በኩል የተቀደሱ ጉባኤዎችን እያከበራችሁ በሌላ በኩል የምትፈጽሙትን አስማታዊ ድርጊት+ መታገሥ አልችልም።

  • ሆሴዕ 6:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 ከመሥዋዕት ይልቅ ታማኝ ፍቅር፣*

      ሙሉ በሙሉ ከሚቃጠል መባም ይልቅ አምላክን ማወቅ ያስደስተኛልና።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ