ዘፀአት 32:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይሖዋም በመቀጠል ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ ግትር* መሆኑን ተመልክቻለሁ።+ 2 ነገሥት 17:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ይሖዋ በነቢያቱ ሁሉና በእያንዳንዱ ባለ ራእይ+ አማካኝነት እስራኤልንና ይሁዳን “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ!+ አባቶቻችሁን ባዘዝኳቸውና በአገልጋዮቼ በነቢያት በኩል ለእናንተ በሰጠሁት ሕግ መሠረት ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ጠብቁ” በማለት በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 14 እነሱ ግን አልሰሙም፤ በአምላካቸው በይሖዋ እንዳላመኑት አባቶቻቸው እነሱም ግትሮች ሆኑ።*+ 2 ዜና መዋዕል 36:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስፍራ ስለራራ መልእክተኞቹን እየላከ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 16 እነሱ ግን የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነድና+ ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ በእውነተኛው አምላክ መልእክተኞች ላይ ያላግጡ፣+ ቃሉን ይንቁና+ በነቢያቱ ላይ ያፌዙ+ ነበር። መዝሙር 78:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ያን ጊዜ እንደ አባቶቻቸውእልኸኛና ዓመፀኛ ትውልድ፣+ደግሞም ልቡ የሚወላውልና*+መንፈሱ ለአምላክ ታማኝ ያልሆነ ትውልድ አይሆኑም። ሕዝቅኤል 3:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 የእስራኤል ቤት ግን ሊሰሙህ አይፈልጉም፤ እኔን መስማት አይፈልጉምና።+ የእስራኤል ቤት ወገኖች ሁሉ ግትርና ልበ ደንዳና ናቸው።+
13 ይሖዋ በነቢያቱ ሁሉና በእያንዳንዱ ባለ ራእይ+ አማካኝነት እስራኤልንና ይሁዳን “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ!+ አባቶቻችሁን ባዘዝኳቸውና በአገልጋዮቼ በነቢያት በኩል ለእናንተ በሰጠሁት ሕግ መሠረት ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ጠብቁ” በማለት በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 14 እነሱ ግን አልሰሙም፤ በአምላካቸው በይሖዋ እንዳላመኑት አባቶቻቸው እነሱም ግትሮች ሆኑ።*+
15 የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስፍራ ስለራራ መልእክተኞቹን እየላከ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 16 እነሱ ግን የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነድና+ ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ በእውነተኛው አምላክ መልእክተኞች ላይ ያላግጡ፣+ ቃሉን ይንቁና+ በነቢያቱ ላይ ያፌዙ+ ነበር።