መዝሙር 98:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሖዋ ማዳኑ እንዲታወቅ አድርጓል፤+በብሔራት ፊት ጽድቁን ገልጧል።+ ኢሳይያስ 11:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በዚያን ቀን የእሴይ ሥር+ ለሕዝቦች ምልክት* ሆኖ ይቆማል።+ ብሔራት ከእሱ መመሪያ ይሻሉ፤*+ማረፊያ ስፍራውም እጅግ የከበረ ይሆናል። ኢሳይያስ 52:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ይሖዋ በብሔራት ሁሉ ፊት ቅዱስ ክንዱን ገልጧል፤+የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ የአምላካችንን የማዳን ሥራዎች* ያያሉ።+ የሐዋርያት ሥራ 13:47 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 47 ይሖዋ* ‘እስከ ምድር ዳር ድረስ መዳንን እንድታመጣ ለብሔራት ብርሃን አድርጌ ሾሜሃለሁ’ በማለት ትእዛዝ ሰጥቶናልና።”+