የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 30:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 30 “ይህ ቃል ሁሉ ይኸውም በፊትህ ያስቀመጥኩት በረከትና እርግማን+ በአንተ ላይ በሚመጣበትና አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ባደረገህ ብሔራት ምድር+ ሆነህ ይህን ቃል ሁሉ በምታስታውስበት* ጊዜ+

  • ዘዳግም 30:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 አምላክህ ይሖዋ ተማርከው የተወሰዱብህን ይመልስልሃል፤+ ምሕረትም ያሳይሃል፤+ እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ካደረገህ ሕዝቦች ምድር ሁሉ መልሶ ይሰበስብሃል።+

  • መዝሙር 30:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  5 ምክንያቱም የሚቆጣው ለአጭር ጊዜ ነው፤+

      ሞገስ የሚያሳየው* ግን ለዕድሜ ልክ ነው።+

      ማታ ለቅሶ ቢሆንም ጠዋት ግን እልልታ ይሆናል።+

  • መዝሙር 106:47
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 47 ይሖዋ አምላካችን ሆይ፣ አድነን፤+

      ደግሞም ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣

      አንተንም በማወደስ ሐሴት እንድናደርግ፣*+

      ከብሔራት ሰብስበን።+

  • ኢሳይያስ 27:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 በዚያም ቀን የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ሰው ዛፍ ላይ ያሉ ፍሬዎችን አርግፎ አንድ በአንድ እንደሚለቅም ሁሉ፣ ይሖዋም ከታላቁ ወንዝ* አንስቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ*+ ድረስ ባለው ቦታ ሁሉ የተበተናችሁትን ይሰበስባችኋል።+

  • ኤርምያስ 29:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በባቢሎን የምትኖሩበት 70 ዓመት ሲፈጸም ትኩረቴን ወደ እናንተ አዞራለሁ፤+ ወደዚህም ስፍራ መልሼ በማምጣት፣ የገባሁትን ቃል እፈጽማለሁ።’+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ