-
ኤርምያስ 50:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
50 ይሖዋ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል ስለ ባቢሎን+ ይኸውም ስለ ከለዳውያን ምድር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦
2 “በብሔራት መካከል ይህን ተናገሩ፤ ደግሞም አውጁ።
ምልክት* አቁሙ፤ ይህን አውጁ።
ምንም ነገር አትደብቁ!
እንዲህም በሉ፦ ‘ባቢሎን ተይዛለች።+
ቤል ኀፍረት ተከናንቧል።+
ሜሮዳክ በፍርሃት ርዷል።
ምስሎቿ ተዋርደዋል።
አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቿ* ተሸብረዋል።’
3 ከሰሜን አንድ ብሔር በእሷ ላይ ተነስቷልና።+
እሱም ምድሪቷን አስፈሪ ቦታ ያደርጋታል፤
በእሷ ውስጥ የሚኖር ሰው የለም።
ሰውም ሆነ እንስሳ ሸሽቷል፤
አካባቢውን ለቀው ሄደዋል።”
-