ኢሳይያስ 15:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 በሞዓብ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+ የሞዓብ ኤር+ በሌሊት ስለወደመችጸጥ ረጭ ብላለች። የሞዓብ ቂር+ በሌሊት ስለወደመችጸጥ ረጭ ብላለች። ኢሳይያስ 15:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ልቤ ስለ ሞዓብ ያለቅሳል። የሚሸሹት የሞዓብ ሰዎች እስከ ዞአርና+ እስከ ኤግላት ሸሊሺያ+ ድረስ ተሰደዱ። እያለቀሱ የሉሂትን ዳገት ይወጣሉ፤በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥፋት የተነሳ ወደ ሆሮናይም በሚወስደው መንገድ ላይ ሲሄዱ ይጮኻሉ።+ ኤርምያስ 48:36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 36 ‘ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት* በሐዘን ያንጎራጉራል፤*+ለቂርሄረስ ሰዎችም ልቤ እንደ ዋሽንት* በሐዘን ያንጎራጉራል።* ያከማቸው ሀብት ይጠፋልና።
5 ልቤ ስለ ሞዓብ ያለቅሳል። የሚሸሹት የሞዓብ ሰዎች እስከ ዞአርና+ እስከ ኤግላት ሸሊሺያ+ ድረስ ተሰደዱ። እያለቀሱ የሉሂትን ዳገት ይወጣሉ፤በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥፋት የተነሳ ወደ ሆሮናይም በሚወስደው መንገድ ላይ ሲሄዱ ይጮኻሉ።+