ኢሳይያስ 60:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ከዚህ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ዓመፅ፣ወይም በክልልሽ ውስጥ ጥፋትና ውድመት አይሰማም።+ ቅጥሮችሽን መዳን፣+ በሮችሽንም ውዳሴ ብለሽ ትጠሪያቸዋለሽ። ኢሳይያስ 65:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ኤርምያስ 23:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በእሱ ዘመን ይሁዳ ይድናል፤+ እስራኤልም ያለስጋት ይኖራል።+ የሚጠራበትም ስም ‘ይሖዋ ጽድቃችን ነው’ የሚል ይሆናል።”+ ሕዝቅኤል 34:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 “‘“ከእነሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤+ አደገኛ የሆኑ የዱር አራዊትንም ከምድሪቱ ላይ አጠፋለሁ፤+ በመሆኑም በምድረ በዳ ያለስጋት ይኖራሉ፤ በጫካዎችም ውስጥ ይተኛሉ።+ ሆሴዕ 2:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በዚያም ቀን ለእነሱ ጥቅም ስል ከዱር አራዊት፣+ከሰማይ ወፎችና መሬት ለመሬት ከሚሳቡ ፍጥረታት ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤+ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤+ያለስጋት እንዲያርፉም* አደርጋለሁ።+
25 “‘“ከእነሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤+ አደገኛ የሆኑ የዱር አራዊትንም ከምድሪቱ ላይ አጠፋለሁ፤+ በመሆኑም በምድረ በዳ ያለስጋት ይኖራሉ፤ በጫካዎችም ውስጥ ይተኛሉ።+
18 በዚያም ቀን ለእነሱ ጥቅም ስል ከዱር አራዊት፣+ከሰማይ ወፎችና መሬት ለመሬት ከሚሳቡ ፍጥረታት ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤+ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤+ያለስጋት እንዲያርፉም* አደርጋለሁ።+