የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 5:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 መለከት ነፊዎቹና ዘማሪዎቹ በኅብረት ይሖዋን ባወደሱና ባመሰገኑ ጊዜ እንዲሁም “እሱ ጥሩ ነውና፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል”+ እያሉ ይሖዋን በማወደስ የመለከቱን፣ የሲምባሉንና የሌሎቹን የሙዚቃ መሣሪያዎች ድምፅ ባሰሙ ጊዜ ቤቱ ይኸውም የይሖዋ ቤት በደመና ተሞልቶ ነበር።+

  • ዕዝራ 3:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 “እሱ ጥሩ ነውና፤ ለእስራኤል የሚያሳየውም ታማኝ ፍቅር ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና”+ በማለት እየተቀባበሉ+ ይሖዋን ማወደስና ማመስገን ጀመሩ። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ የይሖዋ ቤት መሠረት በመጣሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይሖዋን አወደሰ።

  • መዝሙር 106:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 106 ያህን አወድሱ!*

      ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤

      ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+

  • ኢሳይያስ 12:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦

      “ይሖዋን አመስግኑ! ስሙን ጥሩ፤

      ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!+

      ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱን አውጁ።+

  • ሚክያስ 7:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 የርስቱን ቀሪዎች+ ኃጢአት ይቅር የሚል፣ በደላቸውንም የሚያልፍ

      እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው?+

      እሱ ለዘላለም አይቆጣም፤

      ታማኝ ፍቅር በማሳየት ደስ ይሰኛልና።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ