9 ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣
“ሞዓብ እንደ ሰዶም፣+
አሞናውያንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤+
ሳማ የወረሰው ምድርና የጨው ጉድጓድ ይሆናሉ፤ ለዘለቄታውም ባድማ ሆነው ይቀራሉ።+
የሕዝቤ ቀሪዎች ይዘርፏቸዋል፤
ከገዛ ብሔሬ የቀሩት ሰዎችም ይወርሷቸዋል።
10 ከኩራታቸው የተነሳ ይህ ይደርስባቸዋል፤+
ምክንያቱም በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ሕዝብ ላይ ተሳልቀዋል፤ ራሳቸውንም ከፍ ከፍ አድርገዋል።