የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 11:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 እስራኤል ከግብፅ ምድር በወጣበት ጊዜ እንደሆነው ሁሉ፣

      ከሕዝቡ የተረፉት ቀሪዎችም+ ከአሦር የሚወጡበት ጎዳና+ ይኖራል።

  • ኢሳይያስ 65:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 እኔን ለሚፈልገኝ ሕዝቤ፣

      ሳሮን+ የበጎች መሰማሪያ፣

      የአኮርም ሸለቆ*+ የከብቶች ማረፊያ ይሆናል።

  • ኤርምያስ 23:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 “ከዚያም የቀሩትን በጎቼን ከበተንኩባቸው አገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤+ ወደ መሰማሪያቸውም መልሼ አመጣቸዋለሁ፤+ እነሱም ፍሬያማ ይሆናሉ፤ ደግሞም ይበዛሉ።+

  • ኤርምያስ 33:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ከይሁዳ የተማረኩትንና ከእስራኤል የተማረኩትን እመልሳለሁ፤+ እንደቀድሞውም እገነባቸዋለሁ።+

  • ሕዝቅኤል 34:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ጥሩ በሆነ መስክ ላይ አሰማራቸዋለሁ፤ ከፍ ያሉት የእስራኤል ተራሮችም የግጦሽ መሬት ይሆኗቸዋል።+ በዚያም ጥሩ በሆነ የግጦሽ መሬት ላይ ያርፋሉ፤+ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ መስክ ይሰማራሉ።”

  • ሚክያስ 2:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ያዕቆብ ሆይ፣ ሁላችሁንም በእርግጥ እሰበስባለሁ፤

      ከእስራኤል የቀሩትን ያላንዳች ጥርጥር አንድ ላይ እሰበስባለሁ።+

      በጉረኖ ውስጥ እንዳለ በግ፣

      በግጦሽ መስክ ላይ እንዳለም መንጋ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፤+

      ቦታውም በሕዝብ ሁካታ ይሞላል።’+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ